መልካም ዜና
       መምጣት ማየት ነው

የተወደዳችሁ ምእመናን እንደምን አላችሁ? እንኳን አደረሳችሁ?
ዘመናችን በጣም የኦርቶዶክሳውያን ጥቃት እየሰፋ የመጣበት ዘመን ቢሆንም ጨርሰን እንድንጠፋ ያልተወን እግዚአብሔር በልብ መታሰቡ በቃል መነገሩ ከፍ ከፍ ይበል!
በተለያየ ተፈጥሮአዊም ሆነ ሰው ሰራሽ በሆኑ ችግሮች ውድ ሕይወታቸውን ላጡ ምእመናንም ዕረፍተ ነፍስ ያድልልን?
አሁን ያለንበት ዘመን በቤተ ክርስቲያን ላይ የተደራአበ ፈተና እንደጎርፍ የሚጎርፍበት ዘመን መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ 
ሆኖም ግን ፈተና አለ ብለን መንፈሳዊ ሥራ ከመሥራት መቦዘን አይገባምና በሕይወት እስከአለን ድረስ መንቀሳቀስ የግድ ነው፡፡
በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት በሰቆጣ ዙርያ ወረዳ በወለህ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነቅዐ ሕይወት የ፬ቱ ጉባኤ ቤት ከተመሠረተ ሦስተኛ ዓመት የሆነው ሲሆን በእግዚአብሔር ቸርነት በብፁዕ አባታችን መልካም ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ ቀና አመለካከት ከሰቆጣ ማዕከል ማኅበረ ቅዱሳን ጋር አንድ በመሆንና በመተባበር በመጀመሪያ ዓመቱ አካሂዶት የነበረውን የተተኪ መምህራን ስልጠና በሀገራዊ ችግር ምክንያት በሁለተኛው ዓመት ማካሄድ ባይችልም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን በሦስተኛ ዓመቱ እንደገና ለማስኬድ ዝግጅት ላይ ነው፡፡
 በዚህ የስልጠና ቆይታ የሚሰጡ ትምህርቶች:-
1.በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ያለው የመሠረተ ትምህርት ምስጢር 
2.ሥርዓተ ቤተ ክርሽቲያንን መሠረት ያደረጉ የቀቀኖና ትምህርቶች
3.ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት አንፃር የሚተነተኑ ቅብሎሾች
4.ለሰው በጣም አስፈላጊና ዋና የሆነው በዘመናችንም እየከበደ ያለው መንፈሳዊ ትስስር እና ሥነ ምግባራዊ ጉዳይ
5.ከአባቶች እንደ ወረደ ምሥጢረ ሥላሴ የቃል ትምህርት ሆኖ ይቀርባል... ሌላውም በፍቅር ታጅቦ ይሰጣል፡፡
በጣም የሚደነቁበት ደግሞ!
ገና ሲገቡ በመምህራን እግርዎትን ይታጠባሉ፡፡ 
ማረፍያ ይለቀቅልዎታል፡፡
መልካም የሆነ ፊት እያዩ ማዘንዎትን ይረሳሉ፡፡
ከዓለም የወጡ ያህል እስኪሰማዎት ድረስ በመንፈስ ይረካሉ፡፡
ለአንድ ወር ይቀመጣሉ ከተጠቀሙበት የሙሉ እድሜ ስንቅ ይቀስማሉ፡፡
በእውቀት አድገው የአስተሳሰብ ልዕልና አዳብረው በምርቃት ሽኝት እየተደሰቱ ወደበአትዎት ይመለሳሉ፡፡
ይህንንም በተግባር በመግለጽ የሚታይ ሥራ እየሠሩ ለሰማዕትነት ይሽቀዳደማሉ፡፡
ስለዚህ በዞኑም ሆነ ከዞኑ ውጭ ይህን የሚፈልግ ቁጥሩ (30-35) እስኪሞላ አይከለከልም:: ስለሆነም በራሳቸው ወጭ ለምግብ እና ሌሎች ወጮች 3,000 ብር በመክፈል  መሰልጠን የምትፈልጉ  ከወንድም ገ/ሥላሴ(0940832152) እና አሸናፊ(0925017963) እና በየወረዳ ማዕከላችሁ በመደወል እስከ ሐምሌ 04/2014 ዓ.ም  እንድትመዘገቡ። 
ፆታ አይለይም። 
ሥልጠና የሚጀምርበትን ቀን እናሳውቃለን። 
ፎቶ የመጀመርያ ዙር ሰልጣኞች&አሰልጣኞች እና የጉባኤ ቤቱ ገጽታ
( ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን!)

 

Comments powered by CComment