የእዚህ ድረገጽ አላማ እንዲሆን የምንመኘው ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ አንድ ተጨማሪ ድረገጽ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ (website) ማበርከት ነው ፣ በግልም ይሁን ከተለያየ ቦታ ጀማሪ ከሆኑ ክርስቲያኖች የሚቀርቡልንን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከመምህራን ጋር በመሆን በማጣቀሻ የተደገፈ መልስ እንዲያገኙ መርዳት ነው።

በዚህ ድረገጽ ላይ ያካፈልናቸው ድምጾችም ሆኑ መጣጥፎች ለጊዜው ከድምጹ ባለቤቶችም ሆነ ድምጹን ከቀረጹት ባለሞያዎች የተገኘ ምንም አይነት ፈቃድ የለንም። ወደፊት በዚህ ገጽ ለማጋራት ላሰብናቸው መጣጥፎችም እንዲሁ።  ምንም አይነት ንግድና ከትርፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዚህ ገጽ ላይ የማካፈል እቅድ ስለሌለን አላማው ከጅምሩ ግልጽ እንዲሆን እንፈለጋለን። ስለዚህ ድረገጽ አጀማመር ለማወቅ ይህን ይጫኑ። 

ያጋራናቸው ስብከቶችና መጣጥፎች በተፈለገ ጊዜ በቀላሉ ይገኝ ዘንድ በመልክ መልኩ አስቀምጠናል። የረቀቁ ፍለጋዎችን ( advanced search ) መጠቀምም ይቻላል። ተመዝግበን የተለያዩ ስብከቶችን እና መጣትፎችን ማጋራት፤ ጥያቄዎችን መጠየቅና ልምድ ማካፈል ያስችለናል። በተለይም በገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለፋችሁ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቹ ወንድሞችና እህቶች የምትጽፏቸውን መጣጥፎች በዚህ ድረገጽ በማጋራት ተደራሽነታቸውን በማሳደግ ለብዙዎች ህይወት እንዲሆኑ ማድረግ ትችላላችሁ።  እንዳስፈላጊነቱ፣ ለአባላት ብቻ የሚጋሩ ( only registerd memebers)  የተለያዩ ክፍሎችን በመጨመር ልንጠቀም እንችላለን። ለጊዜው ፤ የተመልካች ቁጥሩ 1000 እስኪደርስ አስተያየት ለመሰብሰብ እንዲረዳን ሁሉንም ገጾችህ ከፍት አድርገናቸዋል (  except for the online learning section )

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን፤