ሰላም ጤና ይስጥልን ቸር አላችሁ?
ሰላመ እግዚአብሔር አይለያችሁ?
ጉባኤ ቤታችሁ ወለህ ከጊዜ ወደጊዜ አዳዲስ ነገሮች እየፈጠረ ለሰው የቆመ ትልቅ የርዕይ ባለቤት መሆኑንን እያሳየ ይገኛል፡፡
ደግሞ ምን ተገኘ? የሚል ካለ

በየዓመቱ የሚሰጠው የክረምት ተተኪ መምህራን ሥልጠና እንዳለ ሆኖ 
በዚህ በ2015 ዓ.ም ደግሞ ለወጣቱ እየ ሰጠ ያለውን የዕቅበተ አእምሮ ትምህርት በሕፃናት ላይ መሥራት  አስቦ በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት  ቢሮ መልካም ፈቃድ አግኝቶ ለሙከራ ያህል ከ3ኛ እስከ6ኛ ክፍል  ያሉ 120 ሕፃናትን በሥነ ምግባር በግእዝ ቋንቋና በአብነት ትምህርት ዙሪያ ለማስተማር ምዝገባውን 
የጀመረ መሆኑን ስናሳውቅ በደስታ ነው ምን መሆን እንዳለባቸውና እንዴት መሠራት እንዳለበት ያላችሁን አሳብ ለግሡን ለመፈፀም ዝግጁ ነን፡፡
ሁላችንም እንዲህ የቻልነውን በመሥራት እንመን እንጂ  በመንቀፍ የሚመጣ ለውጥ እንደሌለ እያየን ነው፡፡
ሕፃናት ላይ ባልተሠራበት ምንም ለውጥ አይጠበቅም፡፡
በተሠረቀ አእምሮ ምንም መሥራት ስለማይቻል በአእምሮ ጥበቃ ላይ አጥብቀን እሥራ እላለሁ በየ ቤታቸሁ ሰላም ይግባ፡፡
 በፀጋ ጎልምሱ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ እንጂ ለሆድ አትገዙ፡፡
ሰላም

ይህ በዋግ ኽምራ ዞን አስተዳደር አደራሽ የሚሰጠው የዕቅበተ አእምሮ ጉባኤ ነው በቅርብ ካሉ እንዳይለዩ አደራ፡፡
"የምንሞትለት ዓላማ ከሌለን የምንኖርለት ዓላማ አይኖረንም፡፡"
ለምን እንደምትኖር አስብ ያኔ ሁሉም ግልፅ ይሆናል፡፡

 

ይህ የምታዩት የገጠሩን ምእመን ከተኩላ ለመጠበቅ ማይ ጉንዶ በተባለች ቀበሌ የተደረገ ጉባኤ ነው ሃይማኖታውያን  የሆኑት የዋግ ምእመናን የተፈጥሮ አደራሽ በሆነው በዋግ ዋርካ ስር ቁጭ ብለው ጊዜን ባለመሳሳት የተወደደች ሃይማኖታቸውን እየተማሩ ይታያሉ፡፡ 
መንፈሳዊ ቅንዓት ካለ የግድ ምቹ ቦታ አያስፈልግም ሰው በተገኘበት እየተገኙ ወንጌልን ማስፋፋት ይቻላል ምንም ትራንስፖርት ባይኖር የድምፅ ማጉሊያ ባይዘጋጅም በእግር ተጉዘህ በድምፅ ጩኸህ መልእክትህን ትወጣለህ፡፡
ይህ አሁን ባለፈው እሑድ የተደረገ ጉባኤ ነው፡፡
 አንጀት በሚበላ ትምህርቱን ሲቀበሉ ጭራሽ ድካም አይሰማንም፡፡
የቀረንን ነገር አሟልተን በዘመነ መልኩ ለሕዝቡ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ግን መስተካከል ያለበት ቢኖር፡-
1.የእጅ ማይክ
ማለትም ብዙ ሰው ሲሰበሰብ መድረሽ እየተቻለ ስላልሆነ ተንቀሳቃሽ ማይክ ያስፈልገናል 
2.የትራንስፖርት ጉዳይ 
ይህም ሲባል ጉባኤ ቤቱ የራሱ መኪና ሊኖረው ይገባል ነው ከሠራን ይሆናል ቆርቆሮ አይደል?  
3.ሌሎች ነገሮችን
ማለትም ይህ ያስፈልጋችሗል የምትሉትን ሁሉ በመተባበር አቅርቡ ለግል ጉዳይ  አንጠይቅም ለኅብረት ከመጠየቅ የሚከለክለን የለምና እናሳውቃለን፡፡
እኛ አአምሮ ላይ እንሥራ እናንተ ቁስ ላይ ሥሩ በዋጋው ጊዜ እንገናኛለን፡፡
ለውጥ ማየት የናፈቀው ጉባኤያት ይሥራ በዚሁ መቀጠል የፈለገ በህንፃ ላይ ይሥራ፡፡
ሰላም እንገናኝ!!!

Comments powered by CComment