እንደምን አላችሁ?
ተመልሼ የነበረውን ሪፖርት ይዤ መጣሁ ከእንግዶች ጋር ሁኜ ነው ያዘገየሁት ይቅርታ እናንተም ይቅርታ እንደምታረጉልኝ አምናለሁ!!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አምላክ አሜን!
ሪፖርት ዘወለህ ነቅዐ ሕይወት🌲


በኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን በዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት በሰቆጣ ዙርያ ወረዳ ቤተ ክህነት በ2011 ዓ.ም ሰኔ 17 ቀን /10/ 
በወለህ ደ/ገ/ ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመው የመጻሕፍት አዳሪ ትምህርት ቤት የሁለት ዓመት አጭር ሪፖርት 
መግቢያ
ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በታሪካዊነት እንድትቀጥል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትም ሳትበረዝና ሳትከለስ እስከዘመናችን እንድትደርስ ሙሉ ሐላፊነቱን ወስደው የሠሩት ገዳማትና አድባራት እንዲሁም ጉባኤ ቤቶች ናቸው፡፡


አሁን የሁለተኛ ዓመቱን በአለ ልደት እያከበረ ያለው ጉባኤ ቤታችንም ከነዚህ ባለ ድርሻ አድባራትና ጉባኤ ቤቶች ጋር በዘመን የቀደመ ሆኖ ባይስተካከልም ከዚህ በሗላ ግን ትውፊቱንንና ሥርዓቱን ጠብቆ ለሀገር ብሎም ለዓለም የሚያበርክተው አስተዋጽኦ በቀላል የሚታይ አይደለም ይህ ቀናእያንና መንፈሳውያን በሆኑ ምዕመናን  ጥረት በሀገረ ስብከቱና በሊቀ ጳጳሱ መልካም ፈቃድ በወለህ  የተመሠረተው ጉባኤ የቤተክርስቲያንን ዓላማ ዓላማ አድርጎ እንዲሠራ የተመሠረተ ከእነሱ አንዱ ሆኖ የሚቆጠር ጉባኤ ነው፡፡
ይህም አሁን የሚታየው የጉባኤ ቤቱ ህንፃ  በ2001 ዓ.ም መሠረቱ ተጣለ 2011 ዓ.ም ሰኔ 17 ቀን ደግሞ በብፁዕ አቡነ በርናባስ ቡራኬ የተለመለትን ትምህርት ለመስጠት አሐዱ ብሎ የትምህርት ገበታውን ጀመረ፡፡
ስለዚህ ጉባኤ ቤቱ ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ ለቤተ ክርስቲያን የተሻለ አገልሎትን እየሰጠ ይገኛል በበለጠ መልኩ አቅሙን አጠናክሮ ለወደፊትም እንዲቀጥል ያስችለው ዘንድ እና ለሌላውም አርዐያ እንዲሆን እንዲሁም ዛሬ የሚደረገው ነገር ሁሉ የነገ ታሪክ  እንደመሆኑ መጠን ለትውልድ እንዲተላለፍ ይህንን ዓመታዊ የምሠረታ በአል ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
የጉባኤ ቤቱ አመሠራረት ምክንያት ጉባኤ ቤቱ እንዲመሠረት ያደረጉት ዋና ምክንያቶች ምን እንደሆኑ   የህዋሱ(ኮሚቴው) ሰብሳቢ እንዲህ ይላሉ!
"በ1976 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብ ቆጠራ የኢ/ኦ/ ተ/ቤክርስቲያን ምዕመናን ቁጥር 60 በመቶ የነበረ ሲሆን በ1999 ዓ.ም ደግሞ በተመሳሳይ ቆጠራ   ይህ አሐዝ ቀንሶ 43 በመቶ ደርሷል፡፡ የእዚህም ምክንያቱ
1.የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር መንፈሳዊነት በተላበሱ የሃይማኖት አባቶች ስለማይመራ መንጋው ለነጣቂ ተኩላ እና ለሥነ ምግባር ዝቅጠት የተጋለጠ መሆኑ
2.የሊቃውንት መፍለቂያ የሆኑት የአብነት ትምህርት ቤቶች በመዳከማቸው ዘመኑን የዋጁ አገልጋዮች እጥረት መከሠቱ
3.ከዚህ ሁሉ ጋር ተያይዞ ሉላዊነቱ መንፈሳዊነትን እየዋጠ መምጣቱ እና ሌሎችም ናቸው
ይህንን ችግር ለመፍታት አስተዋጽኦም ለማድረግ በ1992 ዓ.ም በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ  ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ውይይት ተካሂዶ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት እንዲቋቋም መልካም ፈቃዳቸው ቢሆንም ይህ አሳብ ወደተግባር ሳይቀየር 8 ዓመታት በከንቱ አለፉ በመጨረሻም በ2000 ዓ.ም ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከሀገረ ስብከቱ የተጻፈለትን ደብዳቤ  የማጽደቂያ ደብዳቤ በመስጠቱ የግንባታውን ሥራ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ በ1,740,000 ብር ወጭ ለመጨረስ ታቅዶ ግንባታው 2001 ዓ.ም ተጀመረ፡፡
የሀገረ ስብከቱ መልካም ፈቃድ እና የወለህ ደ/ገ/ቅ/ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤና ሕዝበ ክርስቲያኑ በፍጹም ቀናነት ሥራውን ለመጀመር ትልቅ አስተዋጽኦ ቢያደርግም ጉባኤ ቤቱን ዘመኑን በዋጀ መልክ ማሰራት ግን ለብዙ ምዕመናን እንግዳ በመሆኑ ክርስያኖች ለግንባታው የሚገባውን ያህል በሚፈለገው ጊዜ ማድረግ አልቻሉም ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በቂ ልምድ ያላቸው የግንባታ ባለሞያዎች በአካባቢው አለመኖር ሥራው በተገቢው ጊዜ እንዳይጠናቀቅ ምክንያት ሆኗል፡፡ ግንባታው እነዚህን ፈተናዎች አልፎ ወደመጠናቀቅ በደረሰበት ወቅት ብፁዕ አባታችን አቡነ በርናባስ በአደረጉት ክትትል እና ድጋፍ ለዚህ ደረጃ ደርሷል የግንባታውን ሥራ ለማጠናቀቅም 3,633,192 ብር ወጪ ተደርጓል ለመምህራን እና ለደቀ መዛሙርት መገልገያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት ደግሞ 204,800 ብር ፈጅቷል ይህም ወጭ ከአከባቢው ምዕመናን የተደረጉትን ሳይጨምር ነው በመጨረሻም ቤተመጻሕፍት ለማቋቋም በተደረገው ጥረት 74,134 ብር የሚያወጡ 250 መጻሕፍት ተገዝተው እና ተለግሰው አገልግሎት ላይ ውለዋል:: በድምር  3,912,126 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡"
ሀተታ
ሌላም ለዚህ ጉባኤ ቤት ከሚደረጉ ድጋፎች መካከል የዋግ ኸምራ ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንዲሁም የዚሁ ጉባኤ ቤት የበላይ ጠባቂ  የሆኑት አቡነ በርናባስ እስከ ጉባኤው ድረስ በአካል በመገኘት ከሚያደርጉት ልዩ አባታዊ ከሆነ ክትትል ጋሪየሚያደርጉት ድጋፍ በቀላል ሊዘረዘር አይችልም፡፡
ስለሆነም ጉባኤ ቤቱ ከተጀመረ ጀምሮ ከሊቀ ጳጳሱ እስከ ሀገረ ስብከቱ እንዲሁም የመንፈሳዊነት ግዴታቸውን እየተወጡ ያሉ ማኅበራት እና ግለሰቦች ያደረጉት ድጋፍና ጉባኤ ቤቱም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለቤተክርስቲያን እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ በዚህ ሪፖርት በአጭሩም ቢሆን ቀርቧል !!!
ይህ ጉባኤ ቤት ካምፕ የነበረ ቦታ ሲሆን በህዋሱ  ጥረት ለእዚህ  የሚበቃበትን እድል አገኘ  ህንፃው ብቻውን በቂ ስላልሆነ አሁን የልደቱን በአል በፍቅር የሚያከብሩ መምህራን እና ደቀመዛሙርት እንዲገቡ ብፁዕ አባታችን አቡነ በርናባስ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠይቀው የ2.መምህራንና (2000) የ10 ደቀመዛሙርት (400) በጀት እንዲመደብ ተደርጓል፡፡
ይህም ለጊዜው በዞን አቀፍ እንዲያሳትፍ እድል ቢሰጥም ተጨማሪ በጀት ከበጎ አድራጊያን ሲገኝ ግን እንደአገር አቀፍ እንዲያሳትፍ የተደረገ ነው፡፡ አሁን ያለው ጠቅላላ ደቀመዝሙር ፦
-የብሉያት 5
-የሐዲሳት 24
-የሊቃውንት 4 
በድምር 33 ደቀመዛሙርት እየተማሩ ይገኛሉ ፡፡
አስተዋጽኦ
ለዚህ ጉባኤ ቤት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ምዕመናን እና ጉባኤ ቤቱ ለቤተ ክርስቲያን እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ እንደሚከተለው እንመለከታለን:-
ለጉባኤ ቤታችን የተደረጉ የሁለት ዓመት ድጋፎችንም በዝርዝር ስናይ በአራት የተከፈለ ነው፡፡
1.በዕቃ ደረጃ
2.በምግብ ደረጃ
3.በብር ደረጃ
4.ቋሚ ተማሪ በመያዝ
በዕቃ የተደረጉ ድጋፎችና አድራጊ ምዕመናን

1.የ45000 ብር ዕቃ  ማኅበረ ቅዱሳን
2.15 ወንበር የ20000 ብር ምንጣፍ ኩሽና ቤት መሥራት እስከ ጉልበት ማ/ባር ኪ/ምህረት
3.8 ፍራሽ 8  ስጋጃ     1 ቁም ሳጥን ሰቆጣ የሰ/ት አንድነት
4.1 አልጋ       ይስፋ ጌጡ
5.20 ፍራሽ      ገብረ ሃና
6.አልጋ  በሐዊረ ሕይወት ጊዜ በሊቀ ኅሩያን አሳሳቢነት በወጣቶች ኅብረት ትብብር ከሰቆጣ ምዕመናን 
7.  13 ቁም ሳጥን 1 የዳቦ ምጣድ 1 መዝቦልድ አልጋ 10 ሸልፍ  2 የጉባኤ ወንበር 4 ማንበብያ ጠረጴዛ 44 የእንጨት ማንበብያ ወንበር 4 ሰርቢስ እና 2 ሰሐን...በአ.አ ካሉ አባሎቻችን (ከኮሚቴው )
8.    4 የመምህራን  ቤት መጋረጃና የጉባኤ ቤት ሙሉ መጋረጃ 2 ጠረጴዛ ሰቆጣ ወረዳ ማዕከል ማ/ቅዱሳን
9.   25 የጎማ ወንበር 3 ጠረጴዛ ለልደት መዋያ ከተሰበሰበው (እነ እት አበሩ)
10. 35 የጎማ ወንበር አንድ የጎማ ጠረጴዛ ከእሕት ወለተ ጻድቅ (ሐረግ)
11.  የፀጉር መስተካከያ ማሽን ሽብልቅ 17 ወንበር አንድ ምጣድ 35 ሰርቢስ
 12  60 ኩባያ 4 ትሪ ከሰቆጣ  ትምህርት መምርያ የተሰጠንን  ኮምፒተር  ማስጠገን...ከተተኪ መምህራን
13.1 ኮምፒተር  ከ40 በላይ መጻሕፍት በወንድም አሸናፊ አሳሳቢነት 
14.70 ሜትር የውሃ ጎማ ከሰቆጣ ውሃ ልማት
15.2 ወንበር 1 ጠረጴዛ የሚጠገን ኮንፒተር ከሰቆጣ ትምህርት መምርያ
በምግብ ደረጃ  የተደረጉ ድጋፎችና አድራጊ ምዕመናን
1.የ3600 ብር የሚሆን እህል ከብፁዕ አባታችን ከአባታዊ ርኅራኄ ጋር 
2.በዓመት 3 ጊዜ (ዮሐንስ ልደት ትንሣኤ) የበአል መዋያ ፍየል ከሀገረ ስብከቱ ከባለቤትነት ስሜቱ ጋር
3.የቅበላ ሙክት እስከ ጉልበት ሥራ ከገብረ  ሃና 
4.ሽሮ የዳቦ ዱቄት ሌላም ከማኅበረ አርሴማ
5.በተመሳሳይ ከማኅበረ ባር ኪዳነ ምህረት 
6.2 ኩንታል ስንዴ ከሰቆጣ ደ/ገ/  መድኃኔዓለም 
7.1 ኩንታል ስንዴ ከሰቆጣ ደ/ብ ገብርኤል 
8.1 ኩንታል ስዴ ከደ/ፀ/ ወይብላ ማርያም
በብር የተደረጉ ድጋፎችና አድራጊ ምዕመናን
1.4000 ብር ከእህት ገነት ከደሴ
2.2140 ብር ከሰቆጣ መድኃኔ ዓለም
3.2000 ብር ከወይብላ ማርያም
4.2500 ብር ከሰቆጣ ገብርኤል 1600 ብር ቋሚ ነው ከወለተ ኪዳን
5.1800 ብር ከአ.አ ቀሲስ ዳዊት
6.3055 ብር ከመጋቤ ሃዲስ  ንስሐ ልጆች
7.6000 ብር ከማ/ባር ኪ/ምህረት
8.7000 ብር ቋሚ በወር ከአ.አ 
9.300 ለመምህራን 150 ለተማሪዎች በየወሩ ከኮሚቴው
10.300 ብር በየወሩ ለአሥር ተማሪ ድጎማ ከማኅበረ ቅዱሳን /ዋና ማዕከል)
11.10800 ብር ከእስራኤል አገር የተላከ፡፡
ተማሪ በማስተማር የሚደረግ ድጋፍ አድራጊ ምዕመናን 
1.1 ተማሪ ከቤተ ማርያም አ.አ
2.   ""       ከዲ/ ግርማ     ""
3.   ""       ከወንድም ሱራፊ ""
4.   """      ከወንድም ዘመን         ""
5.   """      ከወንድም አስማረ      ""  
6.    ""      ከወንድም ቴዎድሮስ   ""     
7.   """      ከከወንድም በእውቀት
8.   """       ከወልደ ገብርኤል 
9.    ""       ከወለተ ጊዮርጊስ
10.  ""       ከወለተ ማርያም 
11.  ""        ከእማሆይ ዘሐይቅ
12.   ""       ከሂሩት ግርማይ
13.  """       ከገ/ክርስቶስ 
14. 2 ተማሪ  ከማ/ ባር ኪ/ ምህረት 15.   """        ከወለተ ሚካኤል
16.   """         ከክንፈ ገብርኤል
17. 10 ተማሪ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት 
18.4 ተማሪ ደግሞ ስማቸውን ካልገለጡ ከተለያዩ ምዕመናን ከአበርገሌ ወረዳ ማዕከል ማህበረ ቅዱሳን እና ከህብረተሰቡ

ጥያቄ
ጉባኤ ቤትን ለምን እደግፋለሁ?
መልስ
"ጉባኤን መደገፍ አባትህን እንደ መውለድ ነው"
"ተማሪን መርዳትም አባትን እንደማሳደግ ነው"
"ጉባኤ ቤቶች አስተዋይ ሊቃውንትን ኮፒ ማረግያ መሣርያዎች ናቸው"
 "ጉባኤ ቤት የሌላት ቤተ ክርስቲያን ማኅፀን እንደሌላት ሴት ናት"
"ጉባኤን መደገፍ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ማዋለድ ነው"
"ጉባኤ ቤትን ማሰብ እና መርዳት በሊቃውንት ተፈጥሮ ላይ እንደ መሳተፍ  ነው"...ይህ ሁሉ ስለሆነ ጉባኤ ቤትን በመደገፍ ወላጄን ልውለድ! 
ይህ ሁሉ ለጉባኤ ቤቱ ሁሉም የቻለውን ያህል ለመደገፍ እርብርብ እያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ከአካባቢው ምዕመናን ጀምሮ በየትኛውም ቦታ ያሉ ኦርቶዶክሳያን የኛ ነው ብለው የሚያስቡትና እንደ ዓይን ብሌን ለመጠበቅ የሚሯሯጡት ጉባኤ እየሆነ ነው፡፡
ሊቀ ጳጳሱ ሀገረ ስብከቱ እና  በህዋሱ ጥሪ የሚሳተፉ በየከተማው ያሉ ምዕመናን በሰቆጣ ከተማ ያሉ ማኅበራትና እንዲሁም ግለሰቦች የአከባቢው ምእመናንና ክህናት  የሚያደርጉልን ሁሉም  በዚህ አጭር ጽሑፍ ሊቀርብ የማይችል ልዩ ፍቅርና እንክብካቤ የተሞላበት የደስታ ጉዞ ነው፡፡  ይህም  ምንም ይኑረን ምን መኪና ካስፈለገን በየጊዜው በፍቅር ድፍረት የምንጠይቃቸውን ከብፁዕ አባታችን አቡነ በርናባስ ጀምሮ  እነ  አቶ ወልዴን እነ አቶ ስዩምን እነ አቶ አበባውን እነ አቶ ተገኝን እነ አቶ ቻላቸውን ሌሎችንም  ማውሳት ከከቅማችን በላይ ነው፡፡  ሌላው ለበአል ሳይቀር ቤተ ሰብ ትተው ከእኛ ጋር አብሮ እስከመዋል የሚወዱን እነ እህት  አበሩን እነ እህት  ሐረግን መመልከት ልዩ ፀጋ ነው፡፡ምዕመናን ይህን ሁሉ 
ጉባኤውስ ምን ያደርጋል ? ለሚለው ጥያቄ አእምሮአዊ ጥያቄ ስለሆነ መመለስ አለብን 
የጉባኤ ቤቱ አገልግሎት ውስጣዊና ውጫዊ አገልግሎት በሚል በሁለት ተከፍሎ ሊታይ ይችላል
ሀ. ውስጣዊ አገልግሎት 
ውስጣዊ አገልግሎት የምንለው ትምህርት ቤቱ አዳሪ እንደ መሆኑ መጠን በውስጡ ያሉ ለትልቅ ዓለማ የሚጠበቁ ደቀመዛሙርቱን  ለሚጠበቀው  ዓለማው የሚገቡ አድርጎ የሚቀርፅበትና የሚያወጣበት አገልግሎት ነው፡፡  ከእዚህ አገልግሎቱም መካከል፡-
1.መደበኛ የትርጓሜ ትምህርት መስጠት 
2.ራስን በሕይወት እና በጸሎት የመለወጥ ትምህርት (ምክር)
3.ምዕመናንን የሚያንፁበት የስብከት ዘዴ
4.ጥልቀት ያላቸውን ምሥጢራት የሚማሩበት ኮርስ
5.በሁሉም ነገር የጥናት ስልትና ዘዴን እንዲማሩ በር መክፈት 
6. ለዚህም ያመች ዘንድ ደቀ መዛሙርቱን በቡድን ከፍሎ መቆጣጠር 
7.ራሳቸውን በንባብ አሳድገው ሁለ ገብ እውቀት ያላቸው እንዲሆኑ ላይብረሪ አዘጋጅቶ ማበረታታት
8.ዘመናዊ እውቀት ያላቸው ወንድሞችን እሕቶችን ጋብዞ ወቅቱንና ጊዜውን የጠበቀ ስልጠና ማሰጠት
9.የተማሩትን መያዛቸውን አለመያዛቸውን በፈተና መገምገም 
10.ማክሰኞ የቅኔ ምሽት ሐሙስ የንባብ ምሽት በሚል ለሁለንተናዊ ምርምር እንዲበቁ ማድረግ 
11.በወር ውስጥ የሚደረጉ የዝክር ቀናትን የእውቀት የበረከት ማግኛ አድርጎ መጠቀም 
12.ከዚህ ሁሉ ጋር የውስጥ የእርስ በእርስ  ተግባቦት እንዲኖራቸው እና ሲወጡ ከሰው ጋር በፍቅር እንዴት መኖር እንዳለባቸው ማሳየት!!!
ለ. ውጫዊ አገልግሎት
ይህ ውጫዊ አገልግሎት የምንለው  ደግሞ ከጉባኤው አባልነት ውጭ ባሉ ምዕመናን እና ካህናት ለሌሎችም የሚሰጠው አገልግሎት ነው፡፡
ይህም ጊዜያዊ ቋሚ በሚል በሁለት የተከፈለ ነው፡-
ጊዜያዊ የምንለው የጉባኤ ቤቱ መምህራንና ደቀ መዛሙርት በቋሚነት ሳይሆን ለአንድ ጊዜም ሆነ ለሁለት ሂደውም ሆነ ራሳቸው መጥተው የሚሰጠው አገልግሎት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-በዐላትን መሠረት ባደረገ 
             ወቅታዊ ስልጠናን በተመለከተ
             የንስሐ ልጆች ጉዞ
             የማኅበራት ጉዞ....

ቋሚ የምንለው አገልግሎት ጉባኤ ቤቱ በቋሚነት እና በባለቤትነት ሁል ጊዜ የሚሰጠው አገልግሎት ነው፡፡
ለምሳሌ፡-
1.በዙርያው ያሉ 12 ደብሮችን እሑድ እሐድ ሁለት ሁለት መምህራን  ይመድባል
2.ተጀምረው የነበሩ ሰ/ት/ቤቶችን ማፅናት ያልተጀመሩትን ማስጀመር መከታተል
3.በየሦስት ወሩ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ፈጥሮ ማስተማር 
4.በዞኑ ውስጥ ካሉ ወረዳዎች ጠርቶ የወር ስልጠና ሰጥቶ ወንጌልን ተደራሽ ማድረግ 
5.በሰቆጣ ያሉ ማኅበራትን ቋሚ መምህር መድቦ ማስተማር
6.ለሰንበት ት/ቤቶችም ቋሚ የወንጌል ማብራርያ ቅዳሜ ቅዳሜ ይሰጣል (መድኃኔ ዓለም ሰ/ት)
7.ሀገረ ስብከቱ በወደደውና ባመነበት መልካም ፈቃድ ከሰበካ ጉባኤያትና ከሰ/ት/ቤቶች ጋር በመተባበር የሕዝብ ጉባኤያትን ማዘጋጀት
8.በወረዳ በኩልም በየቀበሌው እያመቻቸ ምዕመናንን ያስተምራል
9.በአከባቢው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞችን ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ያስተምራል

10.እንደ ግልም ሆነ እንደ ኀብረት ፈተና ለገጠማቸው ምዕመናን የግል ምክር በመስጠት ለማንኛውም ሰው የመፅናናት ቦታ ለመሆን እየበቃ ይገኛል፡፡
በእዚህ ሁሉ ስብከተ ወንጌልን ለማዳረስ የበኩሉን ድርሻ በመጠኑም ቢሆን እየተወጣ ማለት ነው፡፡ከዚህ የበለጠ እንድናድግና እንድንሠራ አምላከ አበው ይጠብቀን ይጠብቃችሁ!!
ያጋጠሙንን ችግሮች ሁላችሁም ስለምታወቁ ከዚህ ማንሳት አይጠበቅብኝም፡፡  ከአስፈለገም እየተወያየን ይሆናል ማለት ነው፡፡
ስብሐት ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናያት ላዕሌነ!!! አሜን!!!
ተጻፈ በነቅዐ ሕይወት 
ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም
አስታየታችሁን ላኩልን እንዴት እንሂድ????

Comments powered by CComment