የእዚህ ድረገጽ አላማ ወንጌል ለሁሉ እንዲዳረስ አንድ ተጨማሪ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ድረገጽ (website) ማበርከት ነው ፣ በግልም ይሁን ከተለያየ ቦታ ጀማሪ ከሆኑ ክርስቲያኖች የሚቀርቡልንን መንፈሳዊ ጥያቄዎች ከመምህራን ጋር በመሆን በማጣቀሻ የተደገፈ መልስ እንዲያገኙ መርዳት ነው።
ፈቃድበዚህ ድረገጽ ላይ ያካፈልናቸው ድምጾችም ሆኑ መጣጥፎች ከድምጹ ባለቤቶችም ሆነ ድምጹን ከቀረጹት ባለሞያዎች የተገኘ ማረጋገጫ ባይኖርም ጥቂቶቹን መምህራን በስልክ በማግኘት ፈቃደኝነታችውን ገልጽውልናል። ለአብዛኛዎቹ መጣጥፎችና የድምጽ ቅጅዎች አሁንም ቢሆን የፈቃደኝነት ማረጋገጫ ባናገኝም ከ ድረገጹ አላማና ጥቅም አንጻር እነደተለጠፉ እንዲቆዩ አድርገናል። ወደፊት በዚህ ገጽ ለማጋራት ላሰብናቸው መጣጥፎችም እንዲሁ። ምንም አይነት ንግድና ከትርፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በዚህ ገጽ ላይ የማካፈል እቅድ ስለሌለን አላማው ከጅምሩ ግልጽ እንዲሆን እንፈለጋለን። ስለዚህ ድረገጽ አጀማመር ለማወቅ ይህን ይጫኑ።
ያጋራናቸው ስብከቶችና መጣጥፎች በተፈለገ ጊዜ በቀላሉ ይገኝ ዘንድ በመልክ መልኩ አስቀምጠናል። የረቀቁ ፍለጋዎችን ( advanced search ) መጠቀምም ይቻላል። ተመዝግበን የተለያዩ ስብከቶችን እና መጣትፎችን ማጋራት፤ ጥያቄዎችን መጠየቅና ልምድ ማካፈል ያስችለናል። በተለይም በገነት ጽጌ ሰንበት ትምህርት ቤት ያለፋችሁ እግዚአብሔር ጸጋውን ያበዛላቹ ወንድሞችና እህቶች የምትጽፏቸውን መጣጥፎች በዚህ ድረገጽ በማጋራት ተደራሽነታቸውን በማሳደግና ያለስጋት ለብዙ ዘመን እንዲቀመጥ በማድረግ ለብዙዎች ህይወት እንዲሆኑ ማድረግ ትችላላችሁ። ድረገጻችን በመረጃ ቋት የተደገፈ ማህደር ( database driven dynamic website) በመሆኑ በየጊዜው የሚጠበቅ ደጀን ማህደር ( regular cloud based archive and backup)ያለው ስለሆነ ከተለመደው ማህበራዊ ገጾች የተለየ ጥቅም አለው። እንዳስፈላጊነቱ፣ ለአባላት ብቻ የሚጋሩ ( only registered members) የተለያዩ ክፍሎችን በመጨመር ልንጠቀም እንችላለን። ለጊዜው ፤ የተመልካች ቁጥሩ 10000 እስኪደርስ አስተያየት ለመሰብሰብ እንዲረዳን ሁሉንም ገጾችህ ከፍት አድርገናቸዋል ( except for the online learning section )
ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን፤