ጤና ይስጥልኝ የነቅዐ ህይወት ጉባኤ ቤት ቤተሰቦች

ጉባኤ ቤቱ ቃለ ወንጌልን ከማስፋፋት አኳያ ከያዘው አላማ ጋር ተያይዞ በትምህርት ቤቱ ቅጽር ጊቢ ውስጥ የንዋየ ቅድሳት(መጻሕፍት) መሸጫ እየገነባ ይገኛል። ለእዚህም ሥራ ማጠናቀቂያ ባለ 32 ጌጅ 28 የጣርያ ቆርቆሮ አስፈልጎታል ።  የአንዱ ዋጋ 650 ብር ነው። ስለእዚህ የተባለውን ወጪ ሸፍነን ስራውን ለማስጀመር ብንተባበር!!!

 

በወለህ ነቅዐ ሕይወት የ4ቱ  ጉባኤ ቤት የሚሠራው አዲሱ የልማት ሱቅ እዚህ ደርሷል ልማት ክፍሉም የሱቁ ቤት ባያልቅም ሥራውን በቤቱ ሆኖ ጀምሯል በርታ በሉት
 ነገሩ እርፍ ይዞ ወደኋላ ማረስ የለም እንደተባለ ነው። በጥሩ ሁኔታ እንደሚቀጥል  ተስፋ እናደርጋለን።
ለአንድ ጉባኤ ቤት ሦስት ነገሮች ያስፈልጉታል ብለን በማመን ሦስት መርሖች አሉን እኒህም:-
1'እውቀት
2'ሕይወት
3'ልማት ናቸው
አንድ ሰው ለማወቅ ይማራል ባወቀው ይኖራል ለመኖርም ይሠራል ያለማል 
ይህም 
ሊሠራ የማይወድ አይብላ ያለው ነው ምሥጢሩም ሣይሠሩ መብላት በራሱ ሥርቆት ነው ነው።
"ጉባኤ ቤት የቤተ ክርስቲያን ማኅፀን ነው" 
"እናትን መደገፍ ለትውልድ ማሰብ ነው"
"ጉባኤ ቤትን መደገፍ በሊቃውንት ተፈጥሮ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ነው"

Comments powered by CComment