ሰላም ጤና ይስጥልን ተወዳጆች
ይህ በምስሉ የምትመለከቱት የህፃናት ፎቶ በወለህ ነቅዐ ሕይወት የአራቱ ጉባኤያት ትምህርት ቤት የሚማሩት በዕድሜና በሕይወት በእውቀት በሳል የሆኑት አባታችን አባ ገብረ አምላክ በጉባኤ መኖርን መንፈሳዊ ተጋድሎ አድርገው የያዙ ሲሆን በተጨማሪም የአከባቢውን ህፃናት:- 
ፊደል
ንባብ 
ቁጥር
ምሥጢረ ሥላሴ
ሥርዓተ ቅዳሴ
ሥነ ምግባር ሌላውንም እያስተማሩ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡


ጉባኤ ቤቱም ይህ ተግባር ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም መሆኑን ተረድቶ ከበጎ አድራጊ ምዕመናን ጋር በመሆን ሥራውን እያበረታታ ይገኛል::
የላቀች ቤተ ክርስቲያንን ለማየት የሚናፍቅ ሁሉ ይህን መንፈሳዊ ጉዞ በተቻለው መጠን ሊደግፈው ይገባል እንላለን ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ድርሻ እንዳለው ካሰበ የማንሠራው ነገር አይኖርም በተለይ በህፃናት ላይ ሳይሠሩ በመሪዎች ላይ ማጉረምረም በራስ ላይ እንደማበድ ነው፡፡
"ህፃናት ላይ ያልሠራች ቤተ ክርስቲያንም ትልቆች አይኖርዋትም"
"ትልቁ የዓለም ሩጫ በህፃናት አእምሮ ላይ ነው"
"ህፃናት ላይ መሥራት ችግኝ ጣቢያ ላይ እንደመሥራት ነው"
"በዚህ ዘመን በህፃናት አእምሮ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት መቻል ብልህነት ነው" እንላለን 
ለህፃናት ሊደረግ ይገባል የምንለው ድጋፍም:-
ኮቸሮ ሳሙና ምንጣፍ ልብስ ሶላር
ሌላውም ነው ይህን እገዛ በማድረግ ማበራታት ያስፈልጋል እንላለን፡፡
ወለህ ነቅዐ ሕይወት ጉባኤ ቤት

ወለህ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ነቅዓ ሕይወት ጉባኤ ቤት  አባታችን እያስተማሯቸው ካሉ ከ 70 በላይ የአካባቢው ሕጻናት  በከፊል።

Comments powered by CComment